በተርሚናል አገልግሎት የተደራጁኢንተርፕራይዞች የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በተርሚናል አገልግሎት የተደራጁኢንተርፕራይዞች የስራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ።

በአዲስ አበባ   "ምቹ ተርሚናል፤የተሳለጠ አገልግሎት ለወጣቶች ዘላቂ ተጠቃሚነት"በሚል መሪ ሐሳብ  በተርሚናል አገልግሎት የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች   የስራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ ያለውን ብልሹ አሰራር በመቅረፍና ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለመዘርጋት ባደረገው ጥረት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ እንዲደራጁ አድርጓል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማሳለጥና የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና በሰለጠ የሰው ሀይል እንዲመራ ብርቱ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም አውስተዋል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ   ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው   የትራንስፖርት ተርሚናል በርካታ ህዝብ አገልግሎት የሚያገኝበት በመሆኑ ዜጎች ላለአስፈላጊ ወከባና እንግልት ብሎም ለወንጀል እንዳይጋለጡ በዘርፉ የሚሰማሩ ዜጎች ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት በመስራት  ተልዕኮ መወጣት እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

በዚህም ዘርፉ የሚመራበት መመሪያ ከማዘጋጀት ባለፈ ዘርፉ በሰለጠነ የሰው ሀይል እንዲመራና የዜጎችን እንግልትና እሮሮ ለመቅረፍ 996 ዜጎችን በ87 ኢንተርፕራይዞች ማደራጀት መቻሉን ተናግረዋል።

የተርሚናል አገልግሎቱን የተሻለ ለማድረግና ዘርፉ ለዜጎች ተጠቃሚነት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማላቅ የትራንስፓርት አገልግሎት የሚመራበት መመሪያ በማዘጋጀት  በዘርፉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ    ከስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በቅንጅት በመስራቱ በዘርፉ የሰለጠ የሰው ሀይል ስምሪት መስጠቱ የዘርፉን ብልሹ አሰራር ለመቅረፍ አስችሏል ሲሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ  ክቡር አቶ  ያብባል አዲስ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ   ከትራንስፖርት ቢሮ እና ከሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በመቀናጀት በዘርፉ ለሚሰማሩ ዜጎች   በስድስቱ ፖሊ ቴክኒክ  ኮሌጆች  በልል ክህሎት፤በስራ አካባቢ ጸጥታ እና ደህንነት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ አሰራር ላይ ያተኮረ ስልጠና  ሰጥቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.