የፒያሳ ነዋሪዎች / ጊዜ የመለሰው ለውጥ❗
የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከጸደቀ ማግስት ጀምሮ “በልዩ ሁኔታ” ክትትል እየተደረገ የሚገኘው የመንገድ ኮሪደር ልማትን በወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ “ሌት ከቀን” እየተሰራ ይገኛል።
በዚህ የልማት ሥራ ያረጁና የተጎሳቆሉ ለአደጋ የተጋለጡና መልሰው መልማት የሚገቡ ቤቶች ፈርሰው መልሶ የማልማት ስራዎች እየተሰሩ ነው። ለዚሁ ዓላማ ከቦታው የሚነሱ ዜጎች ከከተማ ሳይርቁ ባገኙት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑም ተደርጓል።
በጉራራ የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ የሆኑት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ነዋሪ የነበሩ ወ/ሮ ፋንቱ ካባ እንዲህ ይላሉ "የሰው ልጅ በችግር እንዲኖር የተፈረደበት ይመስል ላለፉት አመታት በችግር ኖረናል ዛሬ ደግሞ ቀን ሲወጣልን ከማመስገን በላይ ምን አለ? የምን ስራው የምንበላው፣የምንጸዳዳው ሁሉም እዛው! ዘመድ ከበር እየመለስን ሃዘናችን ደስታችን በወጉ ሳናይ ኑረናል:: ልጅ በወግ ለማሳደግም ተቸግረን ቆይተናል ዛሬ ደግሞ ታሪካችን ተቀይሮ እዚህ ደርሰናል። ተመስገን ምን ይባላል ያለፋት ጊዜ የፒያሳ ኑሮችን ነበር ብሎ አልፏል አዲስ ህይወት አዲስ ተስፋና ሁሉም አዲስ' በማለት ስሜታቸውን አጋርተውናል::
ሌላው የፒያሳ ነዋሪ የነበረው አቶ ለማ ደምሴ የሚከተለውን ብሏል:: "ይህንን ለማመን እቸገራለሁ፣ ግን ደግሞ የሚታይ እውነት ነው፣ ቀደም ሲል የነበረው ህይወቴ ዛሬ ተቀይሯል፣ በቃ አዲስ ህይወት እጀምራለሁ ሁሉም የተሟላ ነገር እዚህ አለ የምተኛበት፣ የምበላበት፣ በወጉ ጽዳቴን የምጠብቅበት ቤት አግኝቻለሁ፣ በቤት አለመመቻቸት ምክንያት ከኔ የራቁ ቤተሰቦቼ ከዛሬ በኃላ አብረውኝ ይኖራሉ ምክንያቱም አሁን ቆንጆ፣ ሰፊ ቤት አለኝ ተመስገን ማየት ማመን ስለሆነ ቀደም ኑሮዬን ያውቁ የነበሩ ቤቴን መጥተው ይጎብኙልኝ" በማለት ተናግሯል::
ለክፋ ነገር ከማበር ይልቅ ለመልካም ነገር መተባበር የህብረተሰባችንን ጥያቄ በተገቢው ምላሽ መስጠት የመንግስት ቀዳሚ ተግባር ነውና በመሆኑም የሰው ልጆች የጋራ ጠላት የሆነውን ድህነት ኃላቀርነትን ለመግታት አብሮ መቆም መስራት ያሻል ። የከተሞች እድገት ለውጥ የበለጠ እንድንጠነክር እንድንተጋ የተሻለች፣ የበለጸገች አዲስ አበባን እንድንፈጥር ያስችለናልና ለለውጧ በጋራ መስራት ቀዳሚ ተግባራችን ይሁን።
መልካም ቀን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.