በመዲናችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናችን በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡

"የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ሀሳብ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች በክፍለ ከተማ ደረጃ የማጠቃለያ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በውይይቱ ወጣቶች በሀገር መንግስት ግንባታ ሂደትና ልማትን ከማፋጠን አኳያ የማይተካ ሚና እንዳላቸውም በቀረበው የማወያያ ሰነድ ላይ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ወጣቶች በተጠቃሚነት ዙሪያ ሥራን ሳይመርጡ እሴት በሚጨምሩ እና ለመለወጥ በሚያስችሉ የሥራ ዘርፎች ላይ  ለመስራት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይም ወጣቶች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች በአግባቡ ለይቶ ደረጃ በደረጃ ምላሽ መስጠት ለነገ የማይባል መሆኑን በውይይቱ የተገለፀ ሲሆን በተለይም የወጣቶችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጉዳይ በመንግስት በኩል ልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ተገልጷል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው እየተመዘገቡ ባሉ ስኬቶችና በመጡ ውጤቶች ላይ  ጉልህ አስተወፅኦ እያደረጉ መሆኑን አንስተው ቀጣይም መንግስት በሚያከናውናቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ የበኩላቸውን ሚና ይበልጥ  አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.