ህብረተሰቡ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት እያደረገ ያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ህብረተሰቡ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን አስተላፏል፡፡

የከተማውን ሠላምና ፀጥታ ስጋት ላይ የሚጥሉ ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሻ እንደሚያደርግ ፖሊስ አያይዞ አስታውቋል፡፡

በመግለጫው እንደተመላከተው መላው የፀጥታ አካላትና ነዋሪው ህዝባችን በመተባበር ባከናወኗቸው ተግባራት የከተማችን ሠላምና ፀጥታ በመረጋገጡ ህብረተሰቡ የዕለት ከዕለት ተግባሩን ያለ ስጋት ማከናወን መቻሉንም ተገልጿል።

ነዋሪው የከተማው የፀጥታ ጉዳይ ይመለከተኛል በሚል መንፈስ አካባቢውን በተራ በመጠበቅ እና ህገ-ወጦችን እጅ ከፍንጅ ይዞ ህግ ፊት የማቅረብ ልምዱ እያደገ በምጣቱ እና የፀጥታ አካላት ባከናወኗቸው ልዩ ልዩ ተግባራት በአዲስ አበባ የወንጀል ቁጥር መቀነስ ተችሏል፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን ድጋፍ እና ተባባሪነት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን እያቀረበ  በደረሱን ጥቆማዎች እና ፖሊስ በጥናት የለያቸዉ ሠላምና ፀጥታን ስጋት ላይ የሚጥሉ ከባድ ወንጀሎችን ማለትም  የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን እንዲሁም ሌሎች የወንጀል ስጋቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠርና አጥፊዎችንና ተባባሪዎቻቸውን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የተጠናከረ  ቁጥጥርና ፍተሻ ለማድረግ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የወንጀል ድርጊቶቹ ይፈፀምባቸዋል ተብለው በሚጠረጠሩ እና በተለዩ በሁሉም  አካባቢዎች የህግ አግባብን ተከትሎ ፍተሻና ብርበራ የሚያደረግ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ እና ወንጀል እንዳይፈፀም ነዋሪው ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ እያሳሰበ የተለመደውን ጥቆማ የመስጠት ተግባር በማጠናከር ለማንኛውም ፖሊሳዊ መረጃ 011-1110111ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 8882 ላይ በመደወልና መረጃና ጥቆማ በመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.