.png)
-"ሙያዊ ኃላፊነትን በመወጣት የዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ታሳቢ ያደረገ ሀገራዊ ተልዕኮን ሊወጣ የሚችል በሀገሩ የሚኮራ ሀገር ወዳድ ትዉልድ መፍጠር ከሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት ይጠበቃል።"የጉብኝቱ ተሳታፊዎች
“የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው"በሚል መሪ ሀሳብ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አካላት በከተማ ደረጃ የመዲናዋን የልማት ስራዎች ጎበኙ
ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚሰሩ እና በከተማ ደረጃ በሚካሔደዉ የማጠቃለያ ዉይይት ላይ ለመሳተፍ የተወከሉ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የማህበረሰብ አንቂዎች እና የሚኒሚዲያ አባላት የመዲናችንን የልማት ስራዎች ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም በቁርጠኛ አቋምና ዉሳኔ የራስን አቅም እና ፀጋዎችን በመጠቀም፣ በከተማዋ ፈርጀ ብዙ የሆኑ የልማት ስራዎች መሠራታቸዉንና ለአገልግሎት መብቃታቸዉን በተጨባጭ ማየት ብቻ ሳይሆን ለሀገርና ለትዉልድ ሁለተናዊ እና ዘለቄታዊ እድገት የሚበጁ አስደማሚ ታሪካዊ ስራዎች መተግበር መቻሉን ማረጋገጣቸዉን ጎብኚዎቹ ገልፀዋል።
አክለዉም የሚዲያ እና ኮሙንኬሽን ሠራዊት የተሠሩ የልማት ስራዎችን በማስተዋወቅ ፣የተዛቡ አመለካከቶችን በመመከት እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ሚናዉ የላቀ በመሆኑ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ሙያዊ ኃላፊነትን በመወጣት ከሀገር ገፅታ ግንባታ ባሻገር የዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ታሳቢ ያደረገ ሀገራዊ ኃላፊነትን ትዉልዱ እንዲወጣ የሚያስችሉት ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸዉም ተናግረዋል።
የተጎበኙትም በከተማዋ የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ በርካታና የተለያዩ የህዝብ መዝናኛ አገልግሎቶች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ተርሚናሎች፣ፖርኮች ፣ፕላዛዎች፣ የተለያዩ የንግድ ዘርፎችን ያቀፉ ማዕከላት ፣ታሪካዊ ቅርሶች እና አደባባዮች፣ የመኪና፣የእግረኛ እና የሳይክል መተላለፊያ መንገዶች ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እና ሠዉ ተኮር ፕሮጀክቶች ናቸዉ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.