
"ራዕያችን በሀገራችን ሁለተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ነዉ፤ለዚህ ራዕይ መሳካት የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አካላት ግንባር ቀደም ኃላፊነት አለባቸዉ።"አቶ ሞገስ ባልቻ
“የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሀገራዊ መግባባት ካስማ ፤የትውልድ ግንባታ መሠረት ነው"በሚል መሪ ሀሳብ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት የማጠቃለያ ዉይይት አካሔዱ፡፡
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በዉይይቱ እንደገለፁት መንግስት ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ በቁርጠኝነት ሀገርን ህዝብን እና እዉነትን በማስቀደም በሀሳብ ልዕልና በሠራቸዉ ስራዎች ለዘመናት ተሻግረዉ የመጡ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስብራቶችን በመጠገን እንደሀገርም ሆነ በከተማ ደረጃ ተጨባጭ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።
በዚህ የብልፅግና ጉዞ የለውጥ ሒደት ባለን የሀሳብ የላይነት ፣የህዝብ ድጋፍ፣የአደረጃጃት እና የተግባር ዉጤት አቅሞቻችንን በድህረ እዉነት ዘመን ግንባር ቀደም ሆኖ መጠቀም እና ሀገረ መንግስት ግንባታን እዉን ማድረግ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ አካላት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
ራዕያችንም ሆነ መዳረሻችን በሀገራችን ሁለተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ነዉ ያሉት የፓርቲዉ ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለዚህ ራዕይ መሳካት የኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ አካላት ግንባር ቀደም ሀላፊነት እንዳለባቸዉ ጭምር አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ በበኩላቸዉ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ሙያ በራሱ ፅኑ ዓላማን የሚጠይቅ ፣የነፍስ ጥሪን የሚሻ እና ሙያዊ ብቃትን የሚፈልግ መሆኑን አዉቀን ስትራቴጂክ ሆነን በሀሳብ የበላይነት የሚያምንና የሚሞግት ትዉልድ ለሀገር ማበርከት ይጠበቅብናል ብለዋል።
አክለዉም እንደ ሠራዊት አቅማችን የሚለካዉ በፈጠርነዉ ምቹ ሁኔታ የተዛቡ አስተሳሰቦችን በመመከት እና ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ በፍጥነት እና በጥራት ማድረስ ተዓማኒነታችንን በህዝብ ልቦና ዉስጥ ማስረፅና ማፅናት ስንችል ነዉ ያሉት ኃላፊዋ ለዚህም ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ በትጋትና በቁርጠኝነት መሥራት ይገባል ብለዋል።
የዉይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በከተማዋ ለታዩ እምርታዊ ለዉጦች የመንግስትና ህዝብ ድምር ዉጤት መሆናቸዉን ገልፀዋል።
አጀንዳ በመስጠት እና በመሸጥ፣ የሀሳብ የበላይነት በመያዝ እና የተዛቡ አመለካከቶችን በመመከት በሀገርና በትዉልድ ግንባታ ላይ የጀመርነዉን ስራ ይበልጥ ዉጤታማ ለማድረግ ዉይይቱ መግባባትን እና እንደ አንድ ዜጋና ሠራዊት ለመስራት አቅም መፍጠሩን በሠጡት አስተያየት ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.