የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እንዲሁ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ የሚከናወነውን የልማት ኮሪዶሮችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል::

በጉብኝቱ ወቅት ማብራሪያ የሰጡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የልማት ኮሪደር ስራዎቹ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ ከማድረግ በተጨማሪ ከተማዋን የሚመጥን የመንገድ ፣ የመብራት ፣ የአረንጏዴ ልማት ፣ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ፣ ምቹ የእግረኛ መንገድ እንዲሁም ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎችን ያካተተ የከተማዋን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳድግ የልማት ስራ መሆኑን ገልጸዋል::

በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፊ የኮሪዶሮች ጥናት በማድረግ የተጀመረው ይህ የልማት ኮሪደር በአምስት ኮሪደሮች ተለይቶ ግንባታው በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ከንቲባ አዳነች አካባቢዎችን ማልማት ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡንም ተጠቃሚ በማድረግ ሰፊ ስራ በመሰራት ላይ እንደሚገኙ እና ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ቅንጅት የታየበት ስራ መሆኑንም ገልጸዋል::

ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው የልማት ኮሪደር ስራውን ስንተገብር ቅድሚያ ለሰው በማለት ከነበሩበት ጎስቋላ የመኖሪያ አካባቢ በማስወጣት በመንግስት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች ጽዱ እና ለመኖር ምቹ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶችን ተገንብተው መረከባቸውን፣ የንግድና የመስሪያ ቦታ ለነበራቸው በተገቢ ቦታ የተሻለ የንግድ ቦታ መሰጠቱን እንዲሁም የግል ይዞታ ለነበራቸው የካሳ ፣ ምትክ ቦታ ፣ የማጏጏዣ እንዲሁም ቤት እስኪገነቡ ድረስ የቤት ኪራይ ክፍያ በማሟላት የልማት ስራው በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል::

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት አመራሮቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን እና ልማት መገንባት ብቻ ሳይሆን ነዋሪውን አካትቶ ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን በሚገባ የሚያሳይ ስራ መሰራቱን መመልከታቸን ገልጸዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.