ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ ከአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ማህበራት ተወካዮች ጋር በወቅታዊ፣ ከተማዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ ።

ምክትል ከንቲባው በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተደረጉ ውይይቶች ለሀገረ መንግስት ግንባታ አወንታዊ ሚና የሚኖራቸው ሀሳቦች መገኘታቸውን ጠቁመው የሲቪል ማህበራት ተወካዮችም ጥንካሬዎች ይበልጥ እንዲጠናከሩ ክፍተቶች ደግሞ እንዲሞሉ ያነሷቸውን ገንቢ ሀሳቦች አድንቀዋል።

ዓለም አቀፍ አንድምታም ያለው የኑሮ ውድነትን ለማቃለል ምርታማነትን ለማሳደግ ፣ የገበያ ሰንሰለቶችን ለማሳጠር እየተደረጉ ከሚገኙ ጥረቶች ባሻገር በተማሪዎች ምገባ አገልግሎት ፣ የተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞችን በመዘርጋት ፣ በትራንስፖርት እና በጤናው ዘርፍ በሚደረጉ ድጎማዎች ፣ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሪፎርም እና በመሳሰሉት ዘላቂ መፍትሄ ላይ ያተኮሩ ርብርቦች እየተደረጉ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል።

በርካታ ችግሮች ወደ ድል እየተቀየሩ ከተማችንም ሀገራችንም በፈጣን ለውጥ ውስጥ እንዲገኙ የሲቪክ ማህበራት ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጃንጥራር ለህዝባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የጋራ ርብርባችንን ልናጠናክር ይገባል የሚል መልከታቸውን አስተላልፈዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው የሀገራችን ኋላቀር የፖለቲካ ባህል እንዲዘምን እና የዲሞክራሲ ባህል ግንባታችን እንዲፋጠን የሲቪክ ማህበራት ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑን ገልፀዋል።

አገልግሎት አሰጣጡን ከሌብነት እና ከብልሹ አሰራሮች ነፃ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ የአሰራር ግልፀኝነትን በመዘርጋት እና ተጠያቂነትን በማስፈን ብርቱ ትግል መጀመሩን የጠቆሙት አቶ ሞገስ ህዝቡም አገልግሎትን በነፃ ካለ እጅ መንሻ የማግኘት መብቱን ለማረጋገጥ ሁሌም ቁርጠኛ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

የውይይቱ ተወካዮች በበኩላቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች እንደመሆናችን መጠን ሁሉንም ማዕከል ያደረገ አሳታፊና ፍትሀዊ ልማት መመዝገቡን ምስክሮች ብለዋል።
 

እንዲሁም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ፣ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ኢትዮጵያን ለማሻገር ፣ የህዝብን ህይወት ለማሻሻል እያደረጉት ለሚገኘው ብርቱ ጥረት የውይይቱ ተሳታፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.