ዛሬ ማምሻውን ከስሎቬኒያ ፕሬዜዳንት ከክብርት ዶ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማምሻውን ከስሎቬኒያ ፕሬዜዳንት ከክብርት ዶ/ር ናታሻ ፒርስ ሙሳር ጋር በመሆን ፒኮክ የከተማችን ግዙፉ ፓርክ ውስጥ ዘመናዊ የንብ ማነቢያ ሰርቶ ማሳያ (Urban Beeking Observatory) ስራ በይፋ አስጀምረናል።

ከተማችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ህይወት ማሻሻል ላይ ያተኮረ ሰፊ ለውጥ እያስመዘገበች ይገኛል ፤የከተማ ግብርና የዚህ አጀንዳ ቁልፍ ምሰሶ ነው። ይህም የምግብ ዋስትናን ማዕከል ያደረገ የአረንጓዴ ልማት ማስፋፋትን ይጨምራል።

ፕሮጀክቶችን በተሳካ መልኩ በማከናወን የህዝባችንን ኑሮ ለመለወጥ ያስችለን ዘንድ ከአለም አቀፍ አጋሮች፣ ኤምባሲዎች እና ሀገሮች  ጋር በንቃት አብረን እንሰራለን።
ለአብነትም  ዛሬ ከክብርት ፕሬዜዳንቷ ጋር በመሆን በይፋ ስራ ያስጀመርነው ፒኮክ የከተማ የንብ ማነቢያ ሰርቶ ማሳያ አንዱ ሲሆን ስሎቬንያ በከተማ ንብ እርባታ የላቀ ልምድ ያላት በመሆኗ ይበልጥ ትብብራችንን ለማጠናከር እንሰራለን።

ልምዳቸዉን በማጋራትና ሀገር በቀል እሳቤያችን  ለመደገፍ ወስነው ተጨባጭ ስራ በመጀመራቸው ፕሬዚዳንት
ናታሻ እና በኢትዮጵያ የስሎቬኒያ አምባሳደር የሆኑትን ክርስቲና ራዴጅ ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.