1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓልን አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ስታዲየም በአቃቂ ቃሊቲና በሌሎችም ክ/ከተማ በሚገኙ መስጂዶች የተደረገው የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀና በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በድምቀት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን  በዓሉን አስመልክቶ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣ በአቃቂ ቃሊቲና በሌሎችም ክ/ከተማ በሚገኙ መስጂዶች ያደረጉት የኢድ ሶላት ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀትና በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ከኢድ ሶላቱ ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የነበሩ መንገዶች ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

የኢድ ሶላቱ በታቀደው መሰረት በሠላም እንዲከናወን ላደረጉ ታዳሚዎች፣ የኃይማኖቱ መሪዎች፣ ከፀጥታ አካሉ ጎን በመቆም የማስተባበር ስራ ሲሰሩ ለነበሩ ወጣቶችና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ ለመላው የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን አቅርቦ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅርና የሠላም እንዲሆንላቸው በድጋሚ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡ 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.