
ዛሬ ለ6ኛ ዙር የሰለጠኑ 2074 ደንብ አስከባሪ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮችን አስመርቀናል።
አዲስ አበባ እጅግ በጣም ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች የምትገኝ ከተማ ስትሆን ፤ ለነዋሪዎቿ እና ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ተመራጭ ትሆን ዘንድ በልማቱ ብቻ ሳይሆን በሰላም፣ ደህንነት፣ ህግ እና ስርዓትን በማስከበር ረገድም ውጤታማ ስራዎች ተመዝግበዋል።
ዛሬ የተመረቃችሁ እና ስምሪት የወሰዳችሁ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮቻችን፣ ዋነኛው የሰላም ባለቤት ከሆነው የከተማችሁ ህዝብ ጋር በመሆን የተጣለባችሁን ታላቅ እምነት ይዛችሁ በንድፈ ሀሳብና በተግባር በቀሰማችሁት እውቀትና ክህሎት ህዝባችሁን በቅንነት፣ በታማኝነትና በአገልጋይነት መንፈስ ማገልገል ይጠበቅባችኋል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.