ፒያሳ አርጅታ በወደቀችበት ሰዓት መሪዎቿ አይተዋት ወደቀድሞ ዝናዋ ሊመልሷት ነው። ቀደምት የፒያሳ ነዋሪ
ወርቄ ደበላ/ ይባላሉ በፒያሳ ላለፉት 50 አመታት ኑረዋል ቤተሰብ መስርተው ልጆች አፍረተዋል ፒያሳ ላይ በህይወት ዘመናቸው ሁሉንም አሳልፈዋል ክፋንም ደግንም አይተው ዛሬ ላይ ደርሰዋል ።
ዛሬ ከአጠገባቸው 2 የልጅ ልጆች ይኖራሉ።
እርጅና በተጫጫነው አንደበታቸው እድሜዬን በችግር አሳለፍኩ ሹፌሮች ሰፈር ሁሉም ያውቀኛል።
ልጅ ወልጄ አልተባረኩም ልጆቼን ተነጥቄ የትዳር አጋሬ እዛው አጣሁ የሚደግፈኝ አልነበረኝም በምኖርበት ቤት ከላይ ከታች ውሃ እየፈሰሰብኝ ወድቄ እየተነሳሁ ዛሬ እዚህ ደርሻለሁ አመሰግናለሁ ።
ያለፈውን ማስታወስ በጭራሽ አልፈልግም ዛሬ ወርቅ ላይ እንደወደኩ ይሰማኛል ጊዜ ዳኛ እውነትም ነው። ይህንን ሃሳባቸውን የልጅ ልጃቸው ወጣቷ ፍሬህይወት ደረጀ አረጋግጣልናለች እናቴን በእንክብካቤ ልጦራት ተስፋችን ለምልሟል እናመሰግናለን ብላናለች።
ወልደሰንበት ተብዬ ይባላሉ 1975 ጀምረው ፒያሳ ላይ ተንሸርሽረዋል ዛሬን ሲናገሩ ፒያሳ ተዳክማና አርጅታ ልትወድቅ ስትል መንግስት ደርሶላታል እኛንም ካለፈው ህይወታችን እንድንማር ዛሬን የተሻለ እንድንኖር መደረጉ ትልቅ ኃላፊነት ለተሸከመ መንግስት ሰበራን የመጠገን ፍቅር የመሰጠት ሓላፊነት ነው።
ቤቴ ጠባብ ነበር ቤቶቹ የወደቁ አንድ ክፍል ቤት ነበር በዚህ ሥኖር ብዙ ውጣውረዶችን አሳልፈናል።ችግሩ ችግር ነው ያውም የሚታይ የአደባባይ ምስጢር አካባቢው ለልማት መፍረሱ ሲነገረን ስግተን ነበር የትም ወስደው ሊጥሏችሁ ብለውን አስፈራሩን ግን ደግሞ ምን አስባችሁልናል ብለን ጠየቅን ቃል ተሰጠን ፤ በቃላቸው መሰረት የምንፈልገውን ብቻ ሳይሆን ካሰብነው በላይ ተደርጎልናል። የቀበሌ ቤት እንዴት ትመርጣላችሁ ብለው ያከላከሉን ነበሩ እነሱ ተስፋ ቢያስቆርጡንም መንግስት በቃሉ መሰረት ያለውን አርጅተን የምናወጋበን ቤት ሰጥቶናል ክብር ይስጥልን።
ወጣት እድሉ ኮርባሽ ይባላል ፒያሳ ከአራዶቹ መንደር ኑርዬን መስርቼ ብኖርም አራዳ እንደሆንኩ የተሰማኝ አሁን ነው አራዳነት በተጎሳቆለ ቤት በተቀደደ ልብስ መኖር አይደለም ያለፈው ህይወታችን የእጅ መታጠቢያና መጸዳጃን ያየነው ዛሬን ነው በወረፋ መጠባበቅ የየእለት ስራችን ነበር ለታመመ ቅርቶ ለጤነኛው የማይመቸው የአኗኗር ዘያችን ዛሬ በልማት ኮሪደሩ የማይፈታው ህልም ተፈቷል ይህ ሃሳብ ላፈለቁ ለተገበሩ ምስጋና ይገባቸዋል።
መልካም ቀን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.