ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ72ኛው የዓለም ቁንጅና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ72ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር ላይ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ስም በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ላደረገችው የዓለም ቁንጅና አሸናፊ (Miss World) ሀሴት ደረጀ ሽልማት አበረከቱ።

ከንቲባዋ ይህንን ሽልማት ያበረከቱት "ሀገር እና ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ውይይት መድረክ ላይ ስሆን፣ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ በዓለም መድረክ ላይ አሸናፊ መሆን እንደምትችል የሀሴት ደረጀ ድል ምስክር ነው ብለዋል። 

ሀሴት ዉጫዊ ብቻ ሳይሆን በርካታ   ዉስጣዊ ቁንጅና እና ብቃት ስላሳየችን ለብዙ ወጣቶች እና ልጆች የእንችላለን ምሳሌት ነች ብለዋል። 

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ቱሪዝም እና ባህል አምባደር ሆና  እድትሰራ ተልእኮ ሰጥተዋታል።

የዓለም ቁንጅና አሸናፊ (Miss World) ሀሴት ደረጀም ለተደረገላት ሽልማት እና ተልእኮ አመስግናለች።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.