.png)
"ሀገር እና ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ከተማ አቀፍ መድረክ ላይ ተገኝተን ከኪነጥበብ ባለሞያዎች ጋር ተወያይተናል።
ኪነጥበብ የሀገርና የትውልድ ግንባታ አምባ መሆኑን በመገንዘብ በከተማችን የምናከናውናቸው የለውጥ ስራዎች የኪነጥበብ ባለሞያዎችን ተሳትፎ ያረጋግጥ ዘንድ በትብብር ለመስራት የተዘጋጀ መድረክ ነዉ።
በዛሬው ዕለትም ከኪነጥበቡ ማህበረሰቡ ጋር ባደረግነው ውይይት በጥንካሬም ሆነ በክፍተት ባነሷቸዉን ሀሳቦች እና ጥያቄውች ላይ የተወያየን ሲሆን በቀጣይ በከተማችን ሁለንተናዊ ለውጦች ዙሪያ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመስራት ተግባብተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.