ዛሬ ሁሉንም ክፍለ ከተማዎች ወክለው ከመጡ የአዲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ሁሉንም ክፍለ ከተማዎች ወክለው ከመጡ የአዲስ አበባ ሴቶች ጋር “የሴቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና “ በሚል መርህ በከተማ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል።

በአዲስ አበባ  የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አቅድን በመስራት ዉጤቶች ተመዝግበዋል። 

ለአብነትም በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች፣ በንግድና አገልግሎት ዘርፎች መሰማራት እንዲችሉ፤ ጀማሪዎችም በእንጀራና  ዳቦ ፋብሪካዎች፣ በአነስተኛና ጥቃቅን፣ በአረንጓዴ ልማትና ከተማ ዉበት፣ በመጋቢ እናትነት፣ በሴፍቲኔት ፕሮግራም ከተረጂነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ በማስቻል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የስራ እድልና ገቢ እንዲያገኙ እድል ተፈጥሮላቸዉ  ኑሯዉን እያሻሉ ለሌሎችም የስራ እድል በመፍጠር ላይ ይገኛሉ።

በየጎዳናዉ ለብዙ ማህበራዊ ስብራት ተጋልጠው የነበሩ እህቶቻችን "ለነገዋ" የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ውስጥ በመገንባት የስነልቦና ህክምና እና የሞያ ስልጠና ወስደው ተጨባጭ እና ምሳሌ በሚሆኑ ስራዎች ላይ ተሰማርተዋል።
ከግል ስራቸዉ በተጨማሪም በከተማችን ዘላቂ ሰላም  እንዲረጋገጥ በሰላም ሰራዊት ስር በመደራጀት እና በሎሎች በርካታ ስራዎቻችን ዉስጥ የጐላ ተሳትፎ በማድረግ ለዉጦች እንዲመዘገቡ አድርገዋል ። 

በየዓመቱ ማገባደጃ ስናደርግ እንደቆየነው ሴቶችን እያወያየን ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ሀሳባቸዉን እና ጥያቄዎቻቸዉን በማዳመጥ ለሚቀጥለዉ በጀት ዓመት እቅድ ግብዓት በመዉሰድ የኢኮኖሚ ጫናዎችን ለማቃለል፣ የማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ሰላማችንን ዘላቂ በማድረግ ለላቀ ወጤት በጋራ እንደምንተጋ ተግባብተናል። 

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.