በአዲስ አበባ ከተማ ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና እየወሰዱ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ 71 ሺህ 966 ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና እየወሰዱ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል::

ከሰኔ 3 እስከ ሰኔ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሚሰጠው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ሙሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ቀድመዉ መጠናቀቃቸዉንም ገልጸዋል፡፡

በተጠቀሰው የፈተና መስጫ ቀናት 71ሺ 966 ተማሪዎች በ194 የፈተና ጣቢያዎች ለፈተናው ይቀመጣሉ፡፡ ፈተናው 6 የትምህርት ዓይነቶችንም ያካተተ ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 10፣ 11 እና 12 እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 03 እና 04/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቀደም ሲል የተገለጸ ሲሆን ለስኬታማነቱም አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸዉን ጠቅሰዋል፡፡

ተፈታኞች በዝግጅት ጊዜ ያገኙትን ዕውቀት ለፈተናው አንዲያውሉና ከኩረጃ የፀዳ የፈተና ጊዜ እንዲያሳልፉ ዶ/ር ዘላለም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ወላጆችና የትምህርት ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.