.png)
ዛሬ "የወጣቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው መድረክ ከአስራ አንዱም የአዲስ አበበባ ክፍለ ከተሞች ከተወጣጡ የወጣቶች ተወካዮች ጋር በሀገራዊ እና ከተማ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል።
ከለውጡ ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ወጣቶች በአካል እና በስነልቦና ተገንብተዉ አስተማማኝ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ለማስቻል በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን እና በውጤቱም ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀውልናል ።
ለአብነትም ከ1400 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች በገንባታቸውን እና ባለፉት 5 ዓመታት ብቻ 1.1 ሚለየን ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድሎችን እንዲያገኙ ለማስቻል ባከናወንነው ስራ የበርካታዎችን ህይወት በተጨባጭ መለወጥ መቻሉን አረጋግጠውልናል።
የከተማችን ወጣቶች የነገዋን ኢትዮጵያ ለመዋጀት ይቻላችሁ ዘንድ ዛሬ ላይ በስነልቦና፣ በአካል ብቃት፣ በእውቀት እና በክህሎት ራሳችሁን በማዘጋጀት እያበረከታችሁ ያላችሁን አስተዋጽኦዎችን ጨምሮ በበጐ ፍቃድ አገልግሎት ለሰራችሁት የተቀደሰ ተግባር በሰላም ሰራዊት ተደራጅታችሁ የከተማችሁን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ እየሰራችሁ ላላችሁት አኩሪ ስራዎች የከተማ አስተዳደራችን በጣም ያመሰግናችኋል።
ለወደፊትም የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ይበልጥ በሚያረጋግጡ አጀንዳዎች ዙሪያ ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራ ላነሰችሁልን ሀሳቦችና ጥያቄዎች የከተማ አስተዳደራችን አቅዶ የሚሰራ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ ።
ለቸራችሁን እውቅናም እናመሰግናለን፤
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.