
“ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖቻችንን መርዳትና መደገፍ ባህል ያደረገች ከተማ መፍጠር ችለናል! አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባለሀብቶችን በማስተባበር በየካ ወረዳ አንድ ተገንብተው የተጠናቀቁ ቤቶችን በዛሬው ዕለት ቁልፍ ለባለቤቶቹ አስረክበዋል።
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ፣ የክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መገርሳ ገላና እና የሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለፁት “ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖቻችንን መርዳትና መደገፍ ባህል ያደረገች ከተማ መፍጠር ችለናል፤ ይህንን በጎ ተግባር አጠናክሮ በማስቀጠል ያለው ለሌለውን በመርዳት ወገኖቻችን ካሉበት ችግር ማላቀቅ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የበጎ ፈቃድ ስራዎች የህሊና እርካታ የምናገኝበት ከመሆኑ በተጨማሪ ለዝቅተኛ ወገኖች ችግራቸው የሚፈታበት ተግባር በመሆኑ የመተባበርና መደጋገፍ ባህልን በማጎልበት በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ አስገንዝበዋል።
በርዬና ዝሀራ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የተገነባው የሶስት አባወራ ቤቶች ሲሆኑ እንያንዳንዳቸው ባለ ሁለት መኝታ እና የጋራ ንፅህና መጠበቂያ ያላቸው ናቸው።
ለባለቤቶቹ የበግ ሙክት ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን በቤት እድሳቱ ለተባበሩ አካላት በምክትል ከንቲባው ምስጋና ተችሯቸዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.