.png)
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጀርመን አደባባይ አካባቢ በመንግስት በጀት በመገንባት ላይ የሚገኙት የመኖሪያ ቤቶች የደረሱበትን ደራጃ ገምግመናል።
ከተጀመረ 9 ወር የሆነዉ ይህ ግንባታ በጥራት እና በፍጥነት ወደ ማጠናቀቂያዉ ላይ በመሆኑ ቀሪ ስራዎችን በመጨረስ ተጨማሪ የቤት አቅርቦት የመጨመር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
በአሁኑ ሰአት ያለዉ የቤት ፍላጐት በመንግስት ብቻ ሊመለስ የሚችል ባለመሆኑ በቤት ግንባታ ስራ ላይ የተሰማራችሁ የግል አልሚዎችም የቤት አቅርቦትን መጨመር የከተማችን ትልቁ ትኩረት መሆኑን በመገንዘብ እና መንግስት እንዲህ በአጭር ጊዜ መገንባት ከቻለ ከግሉ ዘርፍ ከዚህ በላይ ስለሚጠበቅ የጀመራቹሃቸውን ግንባታዎች በፍጥነት እና በጥራት እድታጠናቅቁ እንዲሁም መሬት አጥራችሁ ግንባታ ያልጀመራችሁም በፍጥነት ጀምራችሁ በማጠናቀቅ ለቤት ፈላጊዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አብራችሁን እድንትሰሩ ጥሪዬን እያቀረብኩ የከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊዉን ድጋፍ የሚሰጣችሁ መሆኑንን በድጋሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.