በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብ(online) በሚሰጥባቸው የመፈተኛ ጣቢያዎች የሙከራ ፈተና ተሰጥቷል።

የሙከራ ፈተናውን በተለያዩ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት የሚማሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮች ጋር በመሆን የሙከራ ፈተናው በተሰጠባቸው ጣቢያዎች በመገኘት ሂደቱን ተመልክተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ስኬታማ እንዲሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን የቅርብ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በዛሬው የሙከራ ፈተና ኮምፒውተሮች ፣ ታብሌቶች እንዲሁም ላፕቶፖች እና ሌሎች ለፈተናው የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶች ዝግጁ መሆናቸውን የቢሮው ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልጸዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.