.png)
ዛሬ ጠዋት "ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀውን የቴክኒክና ሞያ ቴክኖሎጂ አውደርዕይ በይፋ ከፍተናል።
“ኢትዮጵያ የምትበለጽገው የራሳችንን የሰው ሀይልና የተፈጥሮ ሀብት አቀናጅቶ በማልማት ነው” በሚል ጽኑ አቋም በሰራናቸው ስራዎች የብልጽግና መሰረት እየተጣለ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የቴክኒክና ሞያ ተቋማት ለሀገር ብልፅግና ያላቸውን የማይተካ ሚና በአግባቡ በመገንዘብ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገብ ጀምሯል።
በከተማ አስተዳደሩ እየተከነወኑ ባሉ የልማት ስራዎች ውስጥ የቴክኒክና ሞያ ተቋማት የእጅ ስራ ውጤት የሆኑ የተለያዩ ተኪ እና ጥራት ያላቸዉ ግብዓቶችን ከማቅረብ ጀምሮ የሰለጠነ የሰዉ ሀይል በማፍራት በበርካታ ስራዎች ላይ አሻራቸውን ማሳረፍ መጀመራቸው የሀገራችን ብልጽግና የሚሳካው በቴክኖሎጂ አመንጪ ኢትዮጵያውያን ለመሆኑ ትልቅ አብነት ነው።
ለዛሬው አውደርዕይ የቀረቡትን የቴክኖሎጂ ስራዎች ላይ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ ሰልጣኞችን፣ አሰልጣኞችን፣ ባለሞያዎችን እና መላውን አመራር አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.