
የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እየከወነ መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ የገቢያ ማረጋጋት፣ ኑሮው ውድነት መከላከልና ኢትዮጵያ- አዲስ አበባ ታምርት ከተማ አቀፍ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ጋር የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ።
የኑሮ ውድነት ለመከላከል ከተማ አስተዳደሩ በርካት ስራዎችን እየሰራ መቆየቱ ይታወቃል። ስለሆነም የገበያ ዋጋን ማረጋጋት ላይ ዋነኛ መፍትሄ ለማምጣት ኢ-መደበኛ የንግድ ስራ የሚያካሂዱ የህግ ማዕቀፍና ደንቦች ተዘጋጅተው ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን አቶ ጃንጥራር አባይ ገልፀዋል።
ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አያይዘውም በጥራት፣ በብዛትና በጊዜ ላይ ያተኮረ ስራ በዕቅድ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ በተዘጋጀው የ90 ቀናት ዕቅድ ላይ በጋራ በመወያየት ስኬታማ ስራ በመስራት የህዝብን የኑሮ ውድነት ጥያቄዎችን መመለስ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመከላከልና ገበያን ለማረጋጋት አዳዲስና ሰፋፊ የንግድ ማዕከላትን በመገንባት፣ መደበኛ ያልሆኑ ንግዶችን በመከላከል፣ አምራች ኢንዱስትሪውን በመደገፍ፣ ከተማ ግብርና በማጠናከር እና ንግድና ህብረት ስራ አቅራቢዎችን በመደገፍ በርካታ ስራዎችን በመፈፀሙ የተሻለ ውጤት መመዘገቡንም አብራርተዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.