እንኳን ለ35ኛው የአፍሪካ የሕፃናት ቀን በዓል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንኳን ለ35ኛው የአፍሪካ የሕፃናት ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!

የነገ ሃገር ተረካቢ ሕፃናት እናንተ የመጪው ዘመን ተስፋዎች ሁሉም ሥራችን የናንተን የነገ ህይወት መንገድ ለማቅናት የሚደረግ ነው ፣ የነገ እደገታችሁ እዳ የሌለበት ነፃ ለትውልድ የሞትተርፍ እንዲሆን ከእቅድ እስከ እለት እለት ትግበራችን ለእናተ እንሰራለን : : ለዚህ ነው የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ያስፈለገን ።
 የቀዳማይ ልጅነት ሣምንት እና በአፍሪካ ለ35ኛ እንደ ሃገር ለ34ኛ ጊዜ”የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማነጽ ሕፃናት ተኮር ተግባራትን እናከናውን!”  በሚል መሪ ቃል  ሲከበር  ዛሬ አብሪያችሁ ደስታችሁን ስካፈል አሁንም ቀጣይ ስራዎች እንዳሉብን አደራችንን ሳንዘነጋ ነው::

መንግሥት እና ማኅበረሰቡ እናንተ ሕፃናት ለሃገር ያላችሁ ተስፋ እውን እንዲሆን ከማኅፀን ጀምሮ በሚደረግ እንክብካቤ፣ በአልሚ ምግብ፣ በጨዋታ መማር፣ በትምህርት ቤት ምገባ፣ በቤተሰባዊ ትስስር መልካም ዕድገት እንዲኖራችሁ፣ ሁለንተናዊ መብቶቻችሁ እንዲከበሩ፣ በአገራዊ ግንባታ፣ ልማቶች እና ዕድገቶች ውስጥ የእናንተ የሕፃናት ተሳትፎ እንዲረጋገጥ፣ የሕፃናት ፓርላማ እንዲጠናከርና ዴሞክራሲያዊ አሠራር ልምምድ እንዲኖራችሁ እና ለሃገር ተስፋ ያለው ትውልድ እንድትሆኑ መስራታችንን እንቀጥላለን፣   

የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ እንደሚባለው ዛሬ የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ እንድትሆኑ አድርገን እናሳድጋችኋለን ፤ አገር ተረካቢ ትውድም ሆናችሁ ትሰራላችሁ::
ከተማችሁ ሀገራችሁ ትወዳችኋለች:: ሁሌም ምርጥ ምርጡን ለናንተ !

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.