ለኢትዮጵያ ጤና ሥርዓት በርካታ እሴት እንኳን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለኢትዮጵያ ጤና ሥርዓት በርካታ እሴት እንኳን ደስ አለን!!! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ዛሬ በሀገራችን በአይነቱ ልዩ፣ የላቀ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ 25 ሚለዮን ዶላር /3.5  ቢለዬን ብር/ ወጪ የተደረገበትን“የቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ “ መርቀን ለአገልግሎት ክፍት በማድረጋችን እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። 

ይህ የሜድካል ፕላዛ  በኢትዮጵያ ጤና ሥርዓት  ላይ በርካታ እሴቶችን የሚጨምር በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ ህክምና ተደራሽነትንና ጥራትን ከፍ በማድረግ ከሃገር ውጭ ህክምና የሚያጋጥሙ ወጪዎችን የሚቀንስ ፣በተለይም እንደ ኢትዮዽያ  የመጀመሪያው የአጥንት መሳሳት መመርመሪያ እና በአፍሪካም ደረጃ የመጀመሪያ የሆነዉ የልብ፣ የአንጎል እና በሰውነት ላይ የሚከሰቱ የደም ስር ችግሮችን ያለ ኦፕሬሽን መስራት የሚያስችል AI የተገጠመለት በድምጽ መታዘዝ የሚችል በአይነታቸዉ የመጀመሪያ የሆኑ የህክምና መሳሪያዎች የተገጠሙለት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ።

ከተማችንን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ለሚሰሩት ስራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ሲሆን አበረታች ውጤቶችም እየተመዘገቡ ይገኛሉ ።

የከተማችንን የጤና አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ላይ ከፍተኛ ሚና መጫወት የሚያስችለውን የቤተሳይዳ አሜሪካን ሜዲካል ፕላዛ መስራችና ባለቤት የሆኑትን ሚስ ጄን ሊ ይህንን ዘመኑን የዋጀ የጤና  ተቋም ገንብተው ለአገልግሎት ስላበቁ እያመሰገንኩ፤ በቀጣይ አመት ውስጥ  ለመገንባት ባቀዱት ተጨማሪ የምዕራፍ ሁለት ስራ የከተማ አስተዳደራችን የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን ለማረጋገጥ እወዳለሁ። 

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.