ጥበባት ለሀገር ማንነት እና እድገት ቁልፍ ናቸው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጥበባት ለሀገር ማንነት እና እድገት ቁልፍ ናቸው። ባሕላዊ ሀብትን ጠብቀው ያቆያሉ። ለማኅበራዊ አንደነት አበክረዉ በመስራትም ብዝኃነት ላላቸው ማኅበረሰቦች ድምፅ ይሆናሉ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በትምህርት ረገድም ጥበባት ፈጠራን እና ምክንያታዊ አስተሳሰብን ያሳድጋሉ። በኢኮኖሚ ረገድም ጥበባት ፈጠራን፣ ቱሪዝምን እና ስራ ፈጠራን የመምራት አቅምም አላቸው።

ዛሬ ጠዋት ከመላው ኢትዮጵያ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ የጥበቡ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደናል። ተወካዮቹ በተለያየ ደረጃ እየተካሄደ በመጣውና በዘርፉ ያሉ ቁልፍ ጉዳዮችን ለመለየት በረዳው ሰፊ የውይይት መርሃግብር የተሳተፉ ናቸው። የዛሬው መድረክም የውይይት ግኝቶቹን በማጠናከር የከፍተኛ አመራሩን ትኩረት እና መፍትሔ የሚሹ እንዲሁም በዚህ መስክ የተሰማሩ አካላት ሚናቸውን የሚወጡባቸው ጉዳዮችን በመለየት ላይ ያተኮረ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.