በአዲስ አበባ በመከናወን ላይ የሚገኘው የልማት ኮሪደር ስራን በተመለከተ:-
- የልማት ኮሪደር ስራዎቹ በአምስት ኮሪደሮች ተለይተው ግንባታቸው በመፋጠን ላይ ይገኛል
- የልማት ኮሪደር ስራዎቹ ስድስት ክፍለከተሞችን ያካልላሉ
- የልማት ኮሪደር ስራዎቹ ሲጠናቀቁ ለከተማችን ተጨማሪ ውበት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ገቢም ያስገኛሉ
የልማት ኮሪደር ስራው በዋነኛነት:-
- ከተማዋን የሚመጥን ሰፋፉ የመንገድ አውታሮች ለመፍጠር መንገዶችን የማስፋፋት ስራ
- ወጥ እና ዘመናዊ የመብራት ዝርጋታ
- ለከተማው ተጨማሪ ውበት የሚሰጡ የመንገድ ዳር የአረንጏዴ ልማት ስራዎች
- ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት
- ሰፋፉ እና ምቹ የእግረኛ መንገዶች
- የብስክሌት መንገድ
- ያረጁ ህንጻዎች ጥገና እና ማስዋብ
- በተጨማሪም የልማት ኮሪደር ስራው የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ የሚያሳድግ እንዲሁም ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ቅንጅት የታየበት የልማት ስራ ነው::
በልማት ምክንያት ሲኖሩ ከነበሩበት ጎስቋላ መንደር የተነሱ ነዋሪዎችን በተመለከተ:-
1. የማልማት ስራዎቹ ሳይጀመሩ አስቀድሞ ከነዋሪዎቹ ጋር የምክክር ስራ ተደርጏል
2. በመንግስት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ሲኖሩ ለነበሩ ነዋሪዎች ጽዱ እና ለመኖር ምቹ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች ተላልፈዋል
3. የንግድና የመስሪያ ቦታ ለነበራቸው ነዋሪዎች በተገቢ ቦታ የተሻለ የንግድ ቦታ ተሰጥቷል
4. የግል ይዞታ ለነበራቸው ነዋሪዎች ካሳ እና ምትክ ቦታ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በራሳቸው በኩል ያሉ መስፈርቶች አጠናቅቀው ለሚመጡ ነዋሪዎች በሚመጡበት ጊዜ የሚስተናገዱ ይሆናል:: በተጨማሪም የማጏጏዣ እና ቤታቸውን እስኪገነቡ ድረስ የቤት ኪራይ ክፍያ የሚከፈላቸው ይሆናል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.