
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ማለዳ የ90 ቀናት አንዱ የትኩረት አጀንዳዎች መካከል የሆነውን ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ እና በገቢ አሰባሰብ ላይ የሚነሱ ችግሮችን መቅረፍ ላይ ያተኮረ ግምገማ በማድረግ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የ90 ቀናት የትኩረት አጀንዳዎች አንዱ የሆነው ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ እና በገቢ አሰባሰብ ላይ የሚነሱ ችግሮችን መቅረፍ ላይ ያተኮረ ይህ ንቅናቄው የሁሉም ባለድርሻ ተቋማት መሪዎች በተገኙበት ተገምግሞ ዝርዝር አቅጣጫዎችም ተሰጥተዋል።
በዚህ የንቅናቄ መድረክ በአዲስ አበባ ውስጥ እየተመዘገበ ላለው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች አንዱ እና ዋነኛው መሰረት የሆነው የከተማ አስተዳደሩ ገቢን የመሰብሰብ እና የተሰበሰበዉን ገቢ ለለልማት የማዋል ብቃት እያዳበረ መምጣቱ መሆኑ ተገጿል።
የ2017 በጀት ዓመት ቀሪ ገቢን ፍታዊ በሆነ አግባብ አጠናቅቆ መሰብሰብ ለ2018 መሰረት ነው ያሉት ከንቲባዋ ይህም ይሳካ ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተናበን እና ተቀናጅተን በጋራ መስራት ይገባናል ብለዋል።
እንዲሁም ለ2018 በጀት አመት አመቺ የግብር አሰባሰብ ስርዓት መዘርጋት ፣ ግብር ከፋዩን ማበረታት እና ሰራተኛዉን ማትጋት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.