ትዉልድ ተሻጋሪዉ የፒያሳ መልሶ ማልማት !

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ትዉልድ ተሻጋሪዉ የፒያሳ መልሶ ማልማት !

በመሀል አራዳ ከታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር ተሰናስሎ 3 ግዙፍ እና ዘመናዊ ሞሎች፣ አፓርትመንቶች ከአራዳ ፓርክ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተናበዉ አካባቢዉን ሁሉ አስውበው መንፈሳችንን ሊያድሱ፣ ኢኮኖሚያችንን ሊያነቃቁ ፣ ሰፊ የስራ እድል ሊፈጥሩ እና ተወዳዳሪ ሊያደርጉን በፍጥነት እና በጥራት እየተገነቡ ነዉ።

ሶስቱ የሀገራችንን የግብይት ክፍተት የሚዘጉት ሞሎች በከተማ አስተዳደሩ እና የግል ሴክተር አጋርነት እየተገነቡ ሲሆን እነሱም - የአራዳ ሌግዠሪ ሞል፣አዲስ ግራንድ ሞል እና ኦሊ ሞል ናቸዉ።

ከነዚህ ዉስጥ ዛሬ በአይነቱ ልዩ ፣ ለሀገራችን የመጀመሪያው እና ግዙፍ የሆነውን የአራዳ ሌግዠሪ ሞል ግንባታን የመስክ ላይ ግምገማ አድድርገናል።

ባደረግነው ግምገማም ግንባታው ከተጀመረ ገና 7 ወራትን ያስቆጠረ ቢሆንም ስራው በጥራትና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እየተከናወነ መሆኑን ተገንዝበናል።

ግንባታዉ ሲጠናቀቅ የከተማችንን ገቢ ለማሳደግ፣ የስራ ዕድልን ለመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሪን ለማስገኘት እና ሁሉን አይነት ግብይት ከአንድ ስፍራ ማከናወን የሚያስችል እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያሟላ በመሆኑ ያለው ፋይዳ የጎላ ይሆናል።

አዲስ አሰራርን በመቀበል እና “አብሮ ሰርቶ ዉጤታማ መሆን ይቻላል” ብላችሁ በማመን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በአጋርነት አብራችሁን እየሰራችሁ ያላችሁ የግል ሴክተሮች ከልብ እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.