የፖለቲካ ምኅዳርን መክፈት በ2010 ዓ.ም የወሰ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የፖለቲካ ምኅዳርን መክፈት በ2010 ዓ.ም የወሰንነው ቁልፍ ውሳኔ ነው።

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ረጅም ዘመን ከኖረው ፓርቲዎችን ተቃዋሚ አድርጎ ከመመልከት ህጋዊ ተፎካካሪዎች አድርጎ  በማስተናገድ ዴሞክራሲያዊ ከባቢን ለመፍጠር አበክረን ሰርተናል። ይኽ የአስተሳሰብ ሽግግር ሰላማዊ የፉክክር ባሕል ለኢትዮጵያ መፃዒ ተስፋ አስፈላጊ መሆኑን በማመን ላይ የተመሠረተ ነበር። 

በዚሁ አቋም ተመርተንም ላለፉት አመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተመዘገቡ ፓርቲዎች ጋር ተከታታይ መድረኮችን አስቀጥለን ቆይተናል። ዛሬም በሰሞኑ እያከሄድናቸው ካሉ የባለድርሻ አካላት ውይይቶች አካል የሆነ ውይይት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አድርገናል። ይኽም ከየመጡበት አካባቢ የሚነሱ የተለያዩ ሀሳቦችን በማዳመጥ ግብዓት ለመውሰድ የታለመ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.