.png)
ዛሬ "በአፍሪካ ጥራት ያለውና አካታች የሆነ የህጻናት እድገትን ለማረጋገጥ የጋራ ትብብርን ማጠናከር" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ የህፃናት ክብካቤ እና ጥበቃን የተመለከተ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እያካሄድን ነዉ።
ኮንፍረንሱ አዲስ አበባ እንዲካሄድ የተመረጠዉ ከተማዋ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ስለሆነች ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ህጻናት በአዕምሮ፣ በአካል እና በስነልቦና የተሟላ ዕድገት እንዲጎናጸፉ ለማስቻል የሰራችዉ የተቀናጀ እና አካታች የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም አፍሪካውያን ትምህርት የሚወሰዱበት ውጤታማ ስራ በመሆኑ ጭምር ነው።
እኛም አፍሪካዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተሻለ ነገ ከልብ እንድንሰራ ጥሪ በማቅረብ እስካሁን በከተማችን የሰራናቸዉን ስራዎች ልምድ አጋርተናል።
መድረኩን ያዘጋጀውን የአፍሪካ ህብረት የጤና፣ የሰብዓዊ ጉዳዮችና ማህበራዊ ልማት ኮሚሽንን እያመሰገንኩ፤ ኮንፈረንሱን ለመታደም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጣችሁ ሚንስትሮች ፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች፣ የዘርፉ ባለሞያዎች እና ተመራማሪዎች በከተማችሁ አዲስ አበባ ያላችሁ ቆይታ ያማረ እና የተሳካ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.