.png)
በእግረኞች መንገድ በተሽከርካሪ የሄደው ግለሰብ 100 ሺህ ብር መቀጣቱ ተገለፀ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በልማት ኮሪደር በተሰራው እግረኞች መንገድ ላይ በኮድ 4 ተሽከርካሪ መኪና በመሄድ ደንብ የተላለፈው አሽከርካሪ ከፌደራል ፖሊስ ሲቲዝን ኢንጌጅመንት እና ከአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ ።
ተሽከርካሪው ንብረትነቱ የመንግስት የሆነ የአቃቂ ቃሊቲ ክፋለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ-ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የሚጠቀምበት ሲሆን በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ ግለሰቡ ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር በማዋል 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) ብር ተቀጥቷል ።
ባለስልጣኑ ደንብ የተላለፈው የመንግስት ይሁን የግል ድርጅቶች እና ግለሰቦች ያለዩነት በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.