በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በኮሪደር ልማት ተነሺ የሆኑ 57 የቀበሌ ቤት ነዋሪዎች በዛሬው እለት ወደ ኮንዶሚኒየም ቤታቸው ገብተዋል።
በቂርቆስ ከሜክሲኮ በሳር ቤት፣ ጎተራ ወሎ ሰፈር ያሉ መንገዶችን ለእግረኞች ምቹ የማድረግና የውበት እስታንዳርዳቸውን የማስጠበቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
ለዚህ ይረዳ ዘንድም የጠበቡ ቦታዎችን የማስፋት፣ ለመንገዱ የማይመጥኑ ግንባታዎችን የማፍረስ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
የከተማው ነዋሪዎች መረዳት ያለባቸው በኮሪደር ልማት የሚፈናቀልና አለአግባብ ጉዳት የሚደርስበት ነዋሪ የማይኖር መኖሩን ነው።
ይህ የከተማ አስተዳደሩም ሆነ የክፍለ ከተማው አቋም ነውና ቃሉን አክብሮ በዛሬው እለት የኮሪደሩ ልማት ተነሺ የሆኑ ቄራ አካባቢ የሚገኙ 57 ነዋሪዎች የኮንዶሚኒየም ቤት በመምረጣቸው ዛሬ ወደ ቤታቸው ገብተዋል። የገቡበት ኮንዶሚኒየም የካ ጣፎ ሳይት ነው
በቀጣይም ሌሎች የልማት ተነሺዎችን እንደ ምርጫቸው የማስተናገድ ስራ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.