
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ "የሐሳብ ፈጠራ፤ለብሩህ ነገ" በሚል መሪ ቃል ብሩህ አዲስ-3 የንግድ ፈጠራ ሐሳብ ውድድር የማጠቃለያ መርሀ ግብር አካሔደ
ቢሮዉ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የአካባቢያቸውን ፀጋዎች በመለየት በፈጠራ ሃሳብ በመደገፍ ጥቅም ላይ እንዲያውሉ ለማድረግ በተለያዩ ዙሮች ሲያካሂድ ለቆየዉ ዉድድር የዛሬዉ በከተማ ደረጃ የተካሔደ ማጠቃለያ መድረክ መሆኑ ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በከተማችን እስከ አሁን በተከናወኑ የፈጠራ ስራዎች እና የተገኙ ዉጤቶች በዜጎች ተጠቃሚነትና በሀገር ልማት ላይ የራሳቸዉ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
አክለዉም ከተማ አስተዳደሩ መዲናችን በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች በአፍሪካ ብሎም በዓለም ገበያ ላይ ብቁ ተወዳዳሪ ለማድረግ በተጀመረዉ የብልፅግና ጉዞ የፈጠራ ስራ የላቀ ሚና ያለዉ በመሆኑ ፍጥነት አክለንበት ስራ ፈጣሪዎችን ማበረታታትና መደገፍ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ መሆኑንና ከተማ አስተዳደሩም የጀመረዉን ድጋፍ ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የስራና ክህሎት ቢሮ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸዉ ከተማ አስተዳደሩ ከስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመሆን ለፈጠራ ስራ በሰጠዉ ትኩረት ምህዳሩን በማስፋት በ2015 ዓም የፈጠራ ሀሳብ ያላቸዉን ወጣቶች የሀሳብ ፈጠራ ስራዎቻቸዉን እስከ ፌደራል ድረስ ሁለት ጊዜ በማወዳዳር ዉጤታማ ለዉጥ መምጣቱን ገልፀዋል።
ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች ወደ መድረክ በማምጣት ከቴክኖሎጂ ዓለም ጋር በማቆራኘት ሀሳባቸዉን ወደ ገበያ በማዉጣት ለራሳቸዉና ለሀገር አበርክቶአቸዉን በማላቅ ችግር ፈቺ ዜጋ መፍጠር ዋና ዓላማዉ መሆኑን የቢሮ ኃላፊዉ ገልፀዋል፡፡
በክህሎትና በእዉቀት የዳበረ ብቃት ያለዉ ዜጋ ማፍራት መርህ ተደርጎ ወደ ተግባር በመግባቱ በማሠልጠን፣በመሸለም እና በማብቃት የእዉቀት ክህሎትን በማስጠበቅ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ስራ የፈጠሩ ለሀገር የሚበጁ ትዉልድ ማፍራት ተችሏልም ብለዋል።
አክለዉም በ2017 በጀት ዓመት ለ3ኛ ጊዜ የዚሁ አካል የሆነዉን ብሩህ አዲስ_3 የንግድ ሀሳብ ፈጠራ ዉድድር ከወረዳ 145 ወጣቶች የፈጠራ ስራቸዉን አቅርበዉ በከተማ ደረጃ 30 ወጣቶች ማለፋቸዉ ከእነዚህም 15ቱ ለሀገር አቀፍ ዉድድር የሚቀርቡ ሲሆን ከእነዚህ የዛሬዎቹ 5ቱ ተለይተዉ ለዛሬዉ ዉድድር መቅረባቸዉን ተናግረዋል።
በዚህ መድረክ ከቀረቡት አምስት ተወዳዳሪዎች 3 ምርጥ ከዋክብት ባቀረቡት የንግድ ሀሳብ ፈጠራ 1ኛ/ወጣት ያዕቆብ በላይነህ እና 2ኛ/ወጣት ማዕረግ ዘዉዱ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ እንዲሁም 3ኛ/ወጣት ፈልመታ አብደታ ከአቃቂ በመዉጣታቸዉ ሌሎችን ጨምሮ የገንዘብና የሠርተፍኬት ተሸላሚ ሆነዋል።
በመጨረሻም እንደ ሀገር ለጀመርነዉ ሁለተናዊ የብልፅግና ጉዞ ከተማችን ብዙ እና እምቅ ሀሳቦች ያሏት ወጣቶች ባለቤትና ተስፋዎቿ መሆኗን አዉቀን በአገኘነዉ ልምድ እና ተሞክሮ ይህን ሀብት ይበልጥ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ የቢሮዉ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.