
የንግዱን ማህበረሰብ እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ባወያየንበት ወቅት በቀረቡልን ጥያቄዎች መሰረት መልስ እየሰጠን እንገኛለን ።
አዲስ አባባ ቀን ብቻ ሳይሆን ሌሊትም የሚሰራባት ከተማ እየሆነች ነው ።
ዛሬ ለአዲስና ለማስፋፊያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሚቀርቡ የመስሪያ ቦታ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በገባነው ቃል መሰረት ግልፅ መስፈርት አዉጥተን በመስፈርቱ ቅድሚያ ለሚገባቸዉ አምራቾች ኢንዱስትሪዎች ቁልፍ ርክክብ አድርገናል ::
የመስሪያ ቦታ ቁልፍ የተረከባችሁ አርዓያ የሚሆን ስራ ሰርታችሁ ምርታማነትን በመጨመር እና የስራ እድል በመፍጠር ገበያን ማረጋጋት ይጠበቅባችኋል ፡፡
ያለንን መሬትና የሰው ሃይል ተጠቅመን በእልህ ስኬታማ እንሁን ፤ አምራቾችም ትልቅ ህልም ኖሯችሁ ዉጤታማ ሥራ ከእናንተ ይጠበቃል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.