የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና የአዲስ አበባ ከተማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸም ተገመገመ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጋራ ኮሚቴ የሥራ አፈጻጸሙ የሁለቱም አካላት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ 

የጋራ ኮሚቴው የጋራ መግባባትና ውሳኔ በሚስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጎ የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ 

ኮሚቴው ያከናወናቸው ተግባራትም የአዲስ አበባ ከተማ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ እንደሆነ ነው የተገመገመው፡፡ በኮሪደር ልማቱ የታየው ትብብር እንደ አብነት በጥንካሬ መገምገሙን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡ 
 
በይዞታ ማስተላለፍ እና በካሳ ክፍያ ረገድ ያሉ ችግሮችም የጋራ ኮሚቴው ለመፍታት ስምምት ላይ ደርሷል፡፡ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ይዞታ የሕዝብና የመንግስት ሀብት በመሆኑ በጋራ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የጋራ ኮሚቴው አጽኖት ሰጥቶበታል፡፡ 

ልማትና የላቀ የሕዝብ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ የጋራ ውሳኔዎች በመወሰን የአዲስ አበባ ከተማን በጋራ ለማልማት ትኩረት እንደሚደረግ ነው የጋራ ኮሚቴው የገለጸው፡፡ 
በሁለቱ አካት ባለው የእርስበርስ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያም ሰፊ ግምገማ ከተደረገ በኋላ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ 

የጋራ ኮሚቴው፡- ጥምር የቴክኒካል ኮሚቴው ተጨማሪ ሥራ በሚጠይቁና ያልተፈቱ ችግሮችን ለይቶ እንዲያቀርብ አቅጣጫ በማስቀመጥ ግማገማውን ማጠናቀቁ ገልጿል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.