
አዲስ አበባ፦ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት እየሆነች ያለች ከተማ!
የአፍሪካ ህጻናት ጥበቃ ኮንፈረንስ ላይ እየታደሙ ያሉ የተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ተመራማሪዎች እና ለጋሾች የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ጎብኝተዋል።
ተሳታፊዎቹ የኮሪደር እና አጠቃላይ የከተማ መልሶ ማልማት፣ የአፍሪካ ነጻነት ምልክት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እና የህጻናት ልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝቸዋል።
ለሚዲያዎች አስተያየት የሰጡት ጎብኚዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያከናወነ የሚገኘው ሁለንተናዊ ልማቶች ዜጎችን ማዕከል ያደረጉ፣ የአከባቢ ጥበቃን ያስቀደሙ እና ለትውልድ ተሻጋሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም በእያንዳንዱ የልማት ስራዎች ውስጥ ለህዝብ የጋራ ቦታዎች (Public places) እና የነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ህጻናት የተሰጠው ተጨባጭ ትኩረት ለሁሉም የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ አብነት ነው ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.