ባለስልጣኑ በብስክሌት መንገድ በመኪና የሄደችው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለስልጣኑ በብስክሌት መንገድ በመኪና የሄደችው ግለሰብ 100 ሺህ ብር መቀጣቱ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን  አካባቢ በልማት ኮሪደር በተሰራው በብስክሌት መንገድ ላይ መኪና በማሽከርከር ደንብ የተላለፈችው ግለሰብ ከለሚኩራ ክፍለ ከተማ ከሰላምና ጸጥታ አባላት እና ትራፊክ ማኔጅመንት አባላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ ።

አሽከርካሪዋ በቸልተኝነት ደንብ ተላልፋ የባለስልጣኑ ኦፊሰሮች ክትትልና በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት  ግለሰቧ ከነተሽከርካሪዋ  በቁጥጥር ስር በማዋል 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) ብር ተቀጥታለች ። 

ባለስልጣኑ ደንብ የሚተላለፉ  ድርጅቶች እና ግለሰቦች በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም  አስታውቋል ። 

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች  መረጃ  በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ተቋሙ ጥሪውን ያቀርባል። 

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.