''ቆርጠን ከገባን የማናሳካዉ አንዳችም ስራ የለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

''ቆርጠን ከገባን የማናሳካዉ አንዳችም ስራ የለም '' የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከየካቲት 1/2016 ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም ድረስ በ90 ቀናት ሊሰራ ያቀዳቸዉን የንቅናቄ ስራዎች የአንድ ወር ተኩል እቅድ አፈፃፀሙን በዛሬዉ እለት ከከተማ እስከ ወረዳ ካሉ አመራሮች ጋር ገምግሟል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በአዋቀረዉ የሱፐርቪዥን ቡድን የአንድ ወር ተኩል እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግብረመልስ ላይ ትኩረት አድርጎ ግምገማ አካሄዷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እንደገለፁት በጋራ አቅደን ወደስራ ከገባን ጀምሮ በ1ወር ተኩል የታየዉ አፈፃፀማችን ተስፋ ሰጪ መሆኑንና ለቀጣይ ግብአት የሚሆነን ነዉ ያሉ ሲሆን ይህም ተሞክሮአችን የሚያሳየን ምንግዜም ቆርጠን ከገባን የማናሳካዉ አንዳችም ስራ የለም ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ በምክትል ከንቲባ ና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለፁት በእቅድ የያዝናቸው ስራዎች ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜ ስለቀረን ያሉንን አደረጃጀቶች ተጠቅመን በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው ካስመዘገብነዉ ዉጤት አንፃር አፈፃፀማችን ጥሩ ቢሆንም ካለን አቅምና መስራት ከሚገባን አኳያ ስለሚቀረን ክፍተቶችን አርመን የበለጠ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል ።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በዉይይቱ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል በተማችን የስራ እድል ፈጠራ ማጠናከር፤ፀጋዎቻችን መጠቀም፤የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት የከተማዋን ገቢ ማሳደግ፤ሼዶችን በተገቢዉ ጥቅም ላይ ማዋል፤የሌማት ትሩፋታችንን ማስፋትና አመራሩም በተቀራረበ አፈፃፀም መንፈስ መስራት እንደሚገባው ተገልጿል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.