
በከተማ አስተዳደሩ የምርት አቅርቦትን ለማሻሻል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡-የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ
የገበያ ማረጋጋት፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ግብረ-ሀይል የ90 ቀናት እቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡
ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በከተማ አአስተዳደሩ ሁሉም ክፍለከተሞች የምርት አቅርቦትን ለማሻሻል በከተማ ደረጃ የተቋቋመው ግብረሃይል ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፤በጥራትና በብዛት ምርቶች ወደ ገበያው እንዲገባ በማድረግ የነዋሪውን ጥያቄ የመመለስ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ገበያ ላይ በስፋት አምራቾች እንዲሳተፉ በማድረግ የገበያ መረጋጋት እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡ በዚህም በግብይት ማዕከላት በስፋትና በተሻለ ዋጋ ምርት እየቀረበ መሆኑንም ተመላክቷል፡፡
የገበያ ማረጋጋት፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር እና የኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ግብረ-ሀይል ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ የግብረሃይሉን ስራ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት የግብረሃይሉ ሰብሳቢ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ በሁሉም ግብይት ማዕከላት ለገበያው የሚቀርቡ ምርቶችም በተተመነ ዋጋና ስታንዳርድ ለተጠቃሚው እየተሸጠ መሆኑን ሁሉም ክፍለከተሞች ክትትል እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡
የኑሮ ውድነት ለመከላከል ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ጃንጥራር በኢ-መደበኛ የንግድ ስራ የተሰማሩት ነጋዴዎችም ሰርዓትና ህግን በተከተለ መንገድ እንዲሰሩ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች በማጠናቀቅ ሙሉበሙሉ ተግባራዊ እንዲሆንም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
የምሽት ንግድ በተለይ በዋና መንገዶችና የህዝብ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች በተጠናከረ መልኩ እንዲሰራ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡
በ11ንዱንም ክፍለከተሞች የሚገኙ ዩኒየኖች ምርት እዲኖራቸውና ለሸማች ማህበራት በስፋት እንዲያቀርቡ፤ በከተማ ግብርና የሚመረቱ ምርቶች ለተጠቃሚው እንዲቀርቡ ማድረግ ይገባል፡፡
የግብረሃይሉ ሰብሳቢ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመከላከልና ገበያን ለማረጋጋት አዳዲስና ሰፋፊ የንግድ ማዕከላትን በመገንባት፣ መደበኛ ያልሆኑ ንግዶችን በመከላከል፣ አምራች ኢንዱስትሪውን በመደገፍ፣ ከተማ ግብርና ማጠናከር ፤ ንግድና ህብረት ስራ አቅራቢዎችን በመደገፍ በገበያ ውስጥ የተሳለጠ ግብይት እንዲኖር ህገወጥ ግለሰቦች ምርቶችን እንዳይሰበስቡ ክትትልና ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.