
የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ይሆናል፡፡
የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በሃላ ይፋ ይደረጋል።
የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲሆን የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 3-4/2017 ዓ.ም ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 194 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.