የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሸገር ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በተከናወኑ ተግባራትና በቀጣይ የስራ አቅጣጫ ዙሪያ ውይይት አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሸገር ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በ2017 ዓ/ም በተከናወኑ ተግባራትና በ2018  ዓ/ም ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ በፀጥታው ዘርፍ፤ በንግድ ቁጥጥርና ገበያ ማረጋጋት፣ወንጀልን በመከላከል፣የፀረ-ሰላም ኃይሎች እንቅስቃሴን በማክሸፍ ረገድ እንዲሁም የብሔራዊና ኃይማኖታዊ በዓላት በሰላምና በአብሮነት እንዲከበሩ በማድረግ የተሳካ ቅንጅታዊ ውጤት መመዝገቡ በቀረበው ሪፖርት ተብራርቷል።

በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛ እንዳሉት ለሚያጋጥሙን ችግሮች ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር በመቀናጀትና ፈጣን ምላሽ በመስጠት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ችለናል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የከተማ ልማት ሀገራዊ የለውጥ አስኳል መሆኑን አንስተው አብሮ በመስራት ለዚህ ውጤት በቅተናል ካሉ በኋላ ስለ ሰላም ስንናገር ዘላቂነት ያለው፣ በስነልቦና የተገነባ፣ በህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፤ዜጎች በነጻነት ሰርተው የሚገቡበት፤ የጋራ ህልማችንን የምናሳካበት አፈጻጸም እንዲሆን ጠንክረን እንሰራለን። ግንኙነታችን የሰርክ ተግባር ሆኖ ህዝባዊ መሰረት መያዝ አለበት።

ክቡር ከንቲባው አክለውም በጤና፣ በትምህርት በኢኮኖሚ ማረጋጋትና በኮሪደር ልማት አመርቂ ውጤት የተመዘገው በመተባበርና በመተጋገዝ የፀጥታውን ስራ በማጠናከር ሀገራዊ የእድገት መሰረት ለመጣል በመትጋታችን ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር ትስስር በመፍጠር፤ አቅደን በመስራት፤ ህብረተሰቡን በንቃት በማሳተፍ፤ ወንጀልን በመቀነስ፣ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል፤ የህዝብ ለህዝብ መድረኮችን በማጠናከር የሰላም ሰራዊትና የጋቸና ሲርናን በማስተሳሰር በእህትማማች ከተሞች ሰላምን አጽንተናል፤ ልማታችንን ማስቀጠል ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።

 በተጨማሪም በደንብ ጥት ህገወጥነትን በመከላከል፤ በእሁድ ገበያ ተደራሽነትና የምርት አቅርቦት በጠንካራ የግብይ ስርዓት ስኬት የተመዘገበው የሸገር ከተማ አስተዳደርና አዲስ አበባ ተባብረው በመስራታቸው መሆኑን
ጠቅሰው ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በመረዳት በእቅድ በመመራት ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን።

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የ2017 አፈጻጸምን በመነሻነት በመውሰድ በዘጠና ቀን የሚከናወኑ ስራዎችን በውጤት ለማጀብ፣ በሰው ኃይል መረዳዳትን፣ የቴክኖሎጂና የመረጃ ልውውጥን በማጠናከር የሀገራችንን ልማት የህዝባችንን ደህንነት ማረጋገጥ አለብን ብለወዋል።

በተሰጠው አቅጣጫ ማህበረሰቡን በማሳተፍ፣ የፀጥታ ስራውን ማጠናከር፣ በኮንትሮባንድ ንግድ  ቁጥጥር፣ በሚኒሻና በደንብ ማስከበር ያለውን ቅንጅት ማጠናከር፣በጋቸና ሲርናና በሰላም ሰራዊት ያለውን ትብብር ማስቀጠል፣
በእሁድ ገበያን በማስፋት ኑሮን በማረጋጋት ጤናማና ህጋዊ ግብይት በማረጋገጥ፤የገቢ አሰባሰብን ህጋዊ ማቀፍን በማስፋት ሰላምን፣ ልማትንና ገበያን በጋራ በመጠበቅ፤ ማህበራዊ አብሮነትን በማሳደግ፤ እጅ ለእጅ  ተያይዘን ለማደግ፤በተጠናከረ ትብብር ለመስራት የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በውይይቱ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ተሾመ አዱኛን ጨምሮ የሁለቱም ከተሞች ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዦች የንግድና የገቢዎች ቢሮ አመራሮች፣ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጆች፤ እንዲሁም የሚመለከታቸው  የሁለቱም ከተሞች የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.