ዛሬ ማለዳ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማለዳ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ለቡ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለልማት ከሚኖሩበት አካባቢ ለተነሱ ነዋሪዎች ፣ ለአቅመ ደካሞች እና የሃገር ባለውለታዎች የሚሆኑ ሶስት ባለ አምስት ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎችን ግንባታ አስጀምረናል::

ባለሃብቶችን በማስተባበር የሚገነቡት እነዚህ የመኖሪያ ቤቶች በ90 ቀናት ውስጥ ተጠናቅቀው ለነዋሪዎች የሚተላለፉ ሲሆን በአጠቃላይ 108 አባወራዎችን የቤት ባለቤት የሚያደርጉ ይሆናል::

ከጎዶሎአቸው በማካፈል ለዚህ በጎ ስራ እጃቸውን የዘረጉ ልበ ቀና ባለሃብቶችን በከተማችን ነዋሪዎች ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.