የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር "በመት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" የሚል መሪ ቃል የተሰጠው ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የአረንጓዴ ዐሻራ እጅግ ዘርፈ ብዙ ትርፋቶችን ያስገኘ ስራ ነው። በዚህ ዓመት ከሚተከለው ችግኝ ጋር ከ47.5 ቢሊየን ገደማ እንደርሳለን። ይህም በሚቀጥለው ዓመት ከምንተክለው ጋር  ሲደመር 54 ቢሊየን ልንደርስ ያስችለናል።

በዚህ መርሃ ግብር ያመናችሁ፣የተሳተፋችሁ እጆቻችሁ ጭቃ የነካ፥ የተከላችሁ፥ የተንከባከባችሁ ኢትዮጵያውያን፣በኢትዮጵያ የምትገኙ ዲፕሎማቶች፣ይህንን ህልም የደገፋችሁ የየትኛው ሃገር ዜጎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ፥ እንኳን ደስ ያለን ልላችሁ እወዳለሁ።

ከነገ ጀምሮ በየዕለቱ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ በሆነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍልና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.