
ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ-ልማት ላይ በእግረኞች መንገድ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ የተላልፈው አሽከርካሪ 100 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በቂርቆስ ክፋለ ከተማ ወረዳ 02 ቦሌ ማተሚያ ቤት አካባቢ በተሠራው የኮሪደር ልማት መሰረተ ልማት የእግረኞች መንገድ ላይ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ የተላልፈው አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ፖሊሶች ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ ።
ባለስልጣኑ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ 2 አሽከርካሪዎች ከነ ተሽከርካሪአቸው በቁጥጥር ስር በማዋል አንደኛው 100.000 (አንድ መቶ ሺህ ብር )የተቀጣ ሲሆን ሌላኛው ተሽከርካሪ ተጨማሪ የምርመራ እና የማጣራት ስራ በመሠራት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለሰጠው ጥቆማ እያመሰገነ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን ጉዳት በሚያደርሱት እና ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚሰጠውን ጥቆማ አጠናክሮ በመቀጠል ሀላፊነቱ እንዲወጣ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.