እንኳን ለ2017 ዓ. ም የጋራ አሻራ ማኖር አደ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንኳን ለ2017 ዓ. ም የጋራ አሻራ ማኖር አደረሳችሁ !!ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሀገራችን ዘመን የማይሽረው ታሪክ አስቀምጣለች።

ባለፉ ስድስት ዓመታት ሁሉም ኢትዮጵያዊ 40 ቢሊዮን ችግኝ በመትከል ታሪክ አኑሯል።

በከተማችንም ባለፋት ስድስት ዓመታት 6 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የአረንጓዴ ሽፋናችንን ከ 2 ነጥብ 8 ወደ 22 በመቶ ማድረስ ችለናል። የፅድቀት መጠኑም ከ85 በመቶ በላይ መድረሱን አረጋግጠናል። ይህ ለሁላችንም ኩራት ነዉ።

በአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብራችን የተራቆቱ አካባቢዎች አረንጓዴ ለብሰዋል፤ የነጠፉ ወንዞች እና አካባቢዎች ማንሰራራት ችለዋል። አዲስ አበባችንም ንፁህ ውብ እና የቱሪስት ገቢ ማግኛ መሆን ችላለች።

በከተማ ደረጃ ዛሬ ያስጀመርነው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር ከሸገር ወንዝ በእንጦጦ ፓርክ አስከ ፒኮክ ወንዝ ዳርቻ የሚደርስ 21 ኪ. ሜ ሲሆን፤ 860 ሄክታር መሬት ይሸፍናል ።

በአጠቃላይ ከተማችን ለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 916 ሄክታር ቦታ አዘጋጅታለች። ውድ የከተማችን ነዋሪዎች በወንዝ ዳርቻዎች፣ በጤና ተቋማት ፣ በሃይማኖት ተቋማት ፣ በግል ሴክተሮች እና በጎዳናዎች ለምግብነት የሚውሉ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን በመትከል ኢኮኖሚያችንን እንገንባ ።

እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ህፃን አዋቂ፣ የተማረ ያልተማረ ሳንል ሁሉም ዜጋ በጋራ በመሆን እንትከል ስል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

አዲስ አበባን ለመኖር ምቹ ለማድረግ መስራታችንን እንቀጥላለን።

በመጨረሻም ለዚህ መርሃ ግብር ያለመታከት የሰራችሁ፣ የደገፋችሁ እና ተንከባክባችሁ ያሳደጋችሁ ታሪክ ያመሰግናቹሃል፤ ኢትዮጵያም ታመሰግናችኋለች።

ፈጣሪ አምላክ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.