
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች "በመትከል ማንሰራራት " በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በቀጣይ ክረምት ወራትም አረንጓዴ አሻራን ጨምሮ በሌሎችም የከተማችን ልማቶች የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሃይማኖት አባቶች ገልፀዋል።
በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ማትያስን ጨምሮ ሌሎች ብጹዓን አባቶች፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሰባተኛ ጊዜ "በመትከል ማንሰራራት " በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ በከተማችንም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሰኔ 22 / 2017 ዓ/ም ያስጀመሩት የዘንድሮው የከተማችን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማንሳታቸው የሚታወስ ስሆን ሁሉም የሀይማኖት ተቋማትም በተዘጋጀላቸው ስፍራዎች አሻራቸውን እንዲያኖሩ ይጠበቃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.