ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ90 ቀናት የንቅናቄ ስራ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ90 ቀናት የንቅናቄ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል።

ከንቲባዋ ከ15 ቀናት በፊት ከመላው አመራር ጋር በመወያየት ዝርዝር አቅጣጫ የተሰጠባቸው 18ቱም ከተማ አቀፍ የክረምት ንቅናቄ አጀንዳዎች ዙሪያ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለአብነትም በገበያ ማረጋጋት፣ ስራ ዕድል ፈጠራ፣ ከተማ ግብርናና ሌማት ትሩፋት፣ ገቢ አሰባሰብ፣ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር፣ የሁለተኛ ዙር ኮሪደር ልማት ቀሪ ስራዎችን ቆጥሮ ማጠናቀቅ እና ሌሎች ትላልቅ ፕሮጄክቶች አፈጻጸም ዙሪያ አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን በተደረገው ግምገማ ተረጋግጧል።

በተለይም ደግሞ የህዝባችንን የኑሮ ጫናዎችን ለማቃለል በተሰራው የተቀናጀ ስራ የከተማችን የገበያ ማዕከላት፣ የእሁድ ገበያዎች፣ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ስራዎች፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና መሰል ዘርፎች የምርት አቅርቦት ሰንሰለትን በማሳለጥ ከፍተኛ አበርክቶ እንዲኖራቸው መደረጉም ተገልጿል።

ቀሪ ስራዎችን በተሟላ መልኩ ለማሳካት በየደረጃው ያለው አመራር ለላቀ ውጤት በትብብር እንዲረባረብ አቅጣጫ ተሰጥቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.