ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነገ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነገ ሰኔ 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ የሚገኙት የመንግሥታቸውን የ2017 የዕቅድ አፈፃፃም አስመልክቶ  የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚያነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት ነው፡፡

በኢፌዴሪ ህገ መንግስቱ አንቀፅ 55 ንዑስ አንቀፅ (17) እና  በምክር ቤቱ  የአሰራርና  የአባላት  የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 81 ንዑስ አንቀፅ ( 1 እና 3) መሰረት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራሉ መንግሥት ባለስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈፃሚውን አካል አሰራር የመመርመር፤ የመከታተልና የመቆጣጠር ሥልጣን አለው፡፡   

በዚሁ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌና በምክር ቤቱ የአሰራር ደንብ መሰረት 6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ  ነገ ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሚያካሂደው  42ኛ መደበኛ ስብሰባው ክቡር የኢፌዲሪ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በምክር ቤቱ ተገኝተው  የመንግሥታቸውን  የ2017 በጀት ዓመት  የዕቅድ አፈፃፃም  አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና  ምላሽ የሚሰጡ  ሲሆን የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ምክር ቤቱ እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል ፡፡ 

በጉባኤው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች፤ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች የሚገኙ ሲሆን የጉባኤው ሙሉ ሂደትም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ይሆናል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.