ዛሬ ጠዋት በብስራተ ገብርኤል አካባቢ ለህጻናት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ጠዋት በብስራተ ገብርኤል አካባቢ ለህጻናት እና ወጣቶች የሚሆን የስፖርት ማዘውተሪያ ገንብተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::

የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ በአካልና በአእምሮ ዳብሮ እንዲያድግ በከተማችን የህጻናት መጫወቻዎችን እና የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያዎችን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ላይ እንገኛለን::

በምርጫ ወቅት ቃል በገባነው መሰረት ባለፉት 2 ዓመት ተኩል 1236 ሜዳዎችን ገንብተን ለወጣቶቻችን ክፍት ያደረግን ሲሆን ትናንሽ የልጆች መጫወቻዎችን ጨምሮ 12 ሺሕ ስፖርት ማዘውተሪያዎች ለመገንባት አቅደን እየሰራን እንገኛለን::

ዛሬ ያስመረቅነው የብስራተ ገብርኤል አካባቢ ስፖርት ማዘወተሪያ ማዕከል ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተሰራ ሲሆን በውስጡም የእግር ኳስ መጫወቻ፣ 3 በ 1 ሜዳ፣ የተመልካች አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ነው:: 

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በወጣቶቹ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.