በአራዳ ክፍለ ከተማ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች የምትክ ቦታ ዕጣ የማዉጣት ስነ-ስርኣት ተካሄደ
በአራዳ ክፍለ ከተማ የግል ይዞታ ለነበራቸዉ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች የምትክ ቦታ ዕጣ የማዉጣት ስነ-ስርኣት ተካሂዷል፡፡
በፒያሳ አካባቢ የግል ይዞታ የነበራቸዉ 54 የልማት ተነሺዎች የመኖርያ ቤት መገንቢያ ምትክ መሬት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓት ነው የተካሄደው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት በሚከናወንባቸው ቦታዎች ላይ ለነበሩ ነዋሪዎች፣ ምትክ ቤትና ቦታ እንዲሁም የንግድ እንቅስቃሴ ሲያከናውኑ የነበሩ የኮንቴይነር እና ተለጣፊ ሱቆች ባለቤቶች ምትክ ሱቅ በመስጠት ስራቸውን እንዲቀጥሉ እየተደረገ ነው፡፡
በአካባቢዉ ላይ የግል ይዞታ ለነበራቸዉ ለ54 የልማት ተነሺዎች የምትክ መሬት እጣ መውጣቱን የገለጹት የአራዳ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንደሰን ባንጃ በቀጣይ ቀናት ዉስጥም የቦታ ርክክብ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
እጣዉን ያወጡ ነዋሪዎች በተገባላቸዉ ቃል መሰረት ምትክ ቦታ በማግኘታቸው ደስተኞች መሆናቸዉንም ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.